General News

Ethiopia Records Concrete Results in Tobacco Control Drive

Ethiopia’s food and medicines regulator says tobacco control actions delivered measurable outcomes, including inspections, awareness, and removal of smoking products.

ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት የትምባሆ ቁጥጥር … – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life!. ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት የትምባሆ ቁጥጥር … On May 15, 2026 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ኢትዮጵያ በትምባሆ ቁጥጥር ተጨባጭ ውጤት አስመዝግባለች አለ። የዓለም ከትምባሆ ጭስ ነፃ ቀን በዓለም ለ39ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ ”ለኒኮቲንና ለትምባሆ ሱሰኝነት አጋላጭ የሆኑ ስልቶችን እናጋልጥ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው። ባለስልጣኑ ቀኑን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ ትምባሆ ቁጥጥር ላይ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብሏል፡፡ በዚህም በ8 ክልሎች የትምባሆ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ማቋቋምና የማጠናከር ስራዎች መሰራታቸው ተጠቁሟል፡፡ ወደ 900 ሺህ የሚጠጉ ተቋማት ከትምባሆ ጭስ ነፃ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ፍተሻ መደረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ ለተቋማቱ ባለቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱ ተመላክቷል። በተጨማሪም ለማጨስ ሊውሉ ይችሉ የነበሩ የትምባሆ ቅጠል እና ሲጋራዎችን ማስወገድ መቻሉን ባለስልጣኑ አስታውቋል። የዘንድሮውን የዓለም ከትንባሆ ነጻ ቀን ሲከበር የኒኮቲን እና የትንባሆ ሱስን በጋራ ለመመከት ቃል በመግባት እንደሆነም አመልክቷል። የቁጥጥር ሕጎችን እና የፖሊሲ ክፍተቶችን በመድፈን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የግንዛቤ ንቅናቄውን እንዲያጠናክሩ ጠይቋል። መገናኛ ብዙኃን የኢንዱስትሪውን አሳሳች ማስታወቂያዎች በማጋለጥና ትክክለኛውን የጤና መረጃ ለሕዝብ ተደራሽ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል። FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የተቀናጀ የጤና ዘመቻ በአፋር ክልል… በሽንሌ ከተማ በ100 ሚሊየን ብር የተገነባው ኦክስጅን ፋብሪካ ተመረቀ የሀገር ውስጥ ዜና የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ ነው – ዶ/ር መቅደስ ዳባ የሀገር ውስጥ ዜና በሀገር ውስጥ መድኃኒት የማምረት አቅምን ለማሳደግ… More Stories የተቀናጀ የጤና ዘመቻ በአፋር ክልል… May 11, 2026 በሽንሌ ከተማ በ100 ሚሊየን ብር የተገነባው ኦክስጅን ፋብሪካ ተመረቀ May 6, 2026 የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ ነው –… Apr 28, 2026

World No Tobacco Day, Ethiopia FDA, tobacco control, nicotine addiction, smoke-free institutions, public awareness campaign

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Are you human? Please solve:Captcha


Secret Link