24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፍፃሜ ዛሬ ይከናወናል በአዲስ አበባ

24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች ፍፃሜውን ያገኛል – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life!
24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች ፍፃሜውን ያገኛል On May 17, 2026 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች ይጠናቀቃል። በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ላይ ኢትዮጵያን የወከሉ አትሌቶች የሚካፈሉባቸው 8 የፍፃሜ ውድድሮች ምሽት ላይ ይደረጋሉ። በዚህም አመሻሽ 12:30 ላይ በከፍታ ዝላይ አትሌት ገመዶ አባተ እንዲሁም አመሻሽ 12:40 አትሌት ኦታጌ ኦባንግ በወንዶች የጦር ውርወራ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። ምሽት 1 ሰዓት ላይ ደግሞ በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ሩጫ ላይ አትሌት ወሰኔ አሰፋ እና አትሌት አልማዝ ዮሐንስ የሚሳተፉ ሲሆን÷ ምሽት 1:20 ላይ ደግሞ በ400 ሜትር የሴቶች መሰናክል አትሌት ደራርቱ እኖታ፣ አትሌት እመቤት ተከተል እና አትሌት ባንቻየሁ ተሰማ ኢትዮጵያን ይወክላሉ። እንዲሁም ምሽት 1:50 ላይ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ አትሌት አዳኑ ኔንቆ፣ አትሌት ማህተቤ ፍቃዱ እና አትሌት ደስታ ታደለ ተሳታፊ ናቸው። ምሽት 2 ሰዓት ላይ የ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ሩጫ አትሌት እንዳሻው ረታና አትሌት አሸናፊ ኢማና ሲካፈሉት÷ ምሽት 2:20 ላይ ደግሞ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ አትሌት ሙቢን ሀጂ፣ አትሌት ጀምበሩ ሲሳይ እና አትሌት ገብሩ አብረሃ ተፋላሚ ናቸው። በመጨረሻም ምሽት 3 ሰዓት በ400 ሜትር የሴቶች ሩጫ አትሌት ገነት አየለ፣ አትሌት ምስጋና ኃይሉ፣ አትሌት ትዕግስት አያና እና አትሌት አጃይባ አልዪ ይወዳደራሉ። በውድድሩ ኢትዮጵያ እስካሁን 11 ሜዳሊያዎች አስመዝግባለች። በወርቅነህ ጋሻሁን FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like ኢትዮጵያ በ20 ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር በሁለቱም ጾታ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች ማንቼስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ – ተጠባቂው የፍጻሜ ጨዋታ የፕሪሚየር ሊጉ የወርቅ ዋንጫ ባለቤት… ለ3ኛ ተከታታይ የውድድር ዓመት የፈረንሳይ ሊግ ሻምፒዮን – አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ More Stories ኢትዮጵያ በ20 ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር በሁለቱም ጾታ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች May 16, 2026 ማንቼስተር ሲቲ ወይስ ቼልሲ – ተጠባቂው የፍጻሜ ጨዋታ May 16, 2026 የፕሪሚየር ሊጉ የወርቅ ዋንጫ ባለቤት… May 15, 2026
24ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና, ፍፃሜ ውድድሮች, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ 11 ሜዳሊያዎች, ገመዶ አባተ, ወሰኔ አሰፋ