ethiopia news

ቃላት የማይገልጹት የእናት ፍቅር እና የዕለቱ ታሪክ

የእናቶች ቀን በዓለም ዙሪያ ሲከበር የእናትነትን ታላቅነት፣ መስዋዕትነት እና የረጅም ጊዜ ታሪካዊ አመጣጡ በስፋት ተዳስሷል።

ቃላት የማይገልጹት የእናት ፍቅር…. – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life!. ቃላት የማይገልጹት የእናት ፍቅር… On May 10, 2026 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር፣ ከራስ በላይ የሆነ መውደድ፣ ከትናንት ዛሬ የማይለዋወጥ ርህራሄ፣ የመጀመሪያ የሕይወት መምህር… እናት፡፡ እነዚህን መሰል ሐረጎች ስለ እናት ሲነሳ በብዙዎች አዕምሮ የሚመላለሱ ሃሳቦች ከመሆን አልፈው ፍቅርን ለመግለጽ አቅም ያጥራቸዋል። የእናት ፍቅር በቃላት ሊገለጽ የማይችል በመሆኑ ስለ እናት ለመናገር ቃላት ያጥረናል የሚሉት በርካቶች ናቸው። ስለ እናት ዜማ ተሰርቷል፣ ስንኝ ተቋጥሯል፣ ብዙ ተብሏል፡፡ ግን ብዙዎች ለእናቶቻቸው ያላቸውን ልባዊ ፍቅር በሚገባ የሚገልጹ ሆነው አልተገኙም። እናት ህይወቷን፣ ጉልበቷን፣ ጤናዋን፣ ጊዜዋን፣ ያላትን ሁሉ ያለስስት ለልጇ በፍቅር የሰጠች ባለውለታ ናትና በርግጥም በቃላት መግለጽ ከባድ ይሆናል። እናቶች ፈተና ሳይበግራቸው የማይቻል የሚመስለውን ችለው፥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ዋጋ በመክፈል የግል ፍላጎታቸውን ገድበው ከእኔ ይልቅ ለልጄ በሚል የማያባራ ፍቅር እና ጽናት ልጆችን የማሳደግ ትልቁን ኃላፊነት በጥንካሬና በጀግንነት ይወጣሉ። ለዚህ ፍቅር ተመጣጣኝ የሚሆን ምንም ዓይነት ስጦታ ባይኖርም ፍቅር፣ ውለታ እና መስዋዕትነታቸው የሚዘከርበት የእናቶች ቀን ዛሬ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ታስቦ ይውላል። ዕለቱ ወልደው ላሳደጉ እናቶች ፍቅርና ክብርን ከመግለጽ ባሻገር እንደ እናት በፍቅርና ርህራሄ ላሳደጉ የእንጀራ እናቶች እና እንደ እናት የማሳደግ ኃላፊነትን ለተወጡ ሌሎች ሴቶች ጭምር ፍቅር የሚገለጽበት ነው። በዚህ ቀን እናቶችን በማመስገንና ፍቅርን በመግለጽ፣ ስጦታዎችን በማበርከት እንዲሁም ምግብ ማብሰልን ጨምሮ ከሥራ እንዲያርፉ በማድረግ ይከበራል። በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የእናቶችን ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በማጋራት ፍቅርን መግለጽና ክብር መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡ የእናቶችን ቀን የማክበር ሀሳብ በሺዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት የተጀመረ ሲሆን፥ በ16ኛው ክፍለ ዘመን “የእናት እሑድ” በመባል የሚታወቅ በዓል እንደነበር ይነገራል። ከዚያ በኋላ በፈረንጆቹ 1908 አና ጃርቪስ የተባለች አሜሪካዊት ለእናቷ መታሰቢያነት ባዘጋጀችው ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በተለያዩ የዓለም ሀገራት ለሚከበረው የእናቶች ቀን ምክንያት ሆናለች፡፡ አና ጃርቪስ የጀመረችውን በዓል በአሜሪካ መንግሥት ከ6 ዓመታት በኋላ በይፋ እውቅና ተሰጥቶት የፈረንጆቹ ግንቦት ወር በገባ በሁለተኛው እሁድ መከበር ጀምሯል፡፡ ብዙዎች አድገው ትዳር ከመሰረቱና ልጆች ከወለዱ በኋላም ጭምር እናቶቻቸው የቅርብ አማካሪዎቻቸው፣ የብርታታቸው ምንጭና ደጋፊ ሆነው ይቀጥላሉ። መልካም የእናቶች ቀን FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የእናት ውለታዋ … ብዙነሽ በቀለ በሙዚቃዎቹ ፍቅር እና እርቅን ሲሰብክ የኖረው አሊ ቢራ… ሁለቱ የጥበብ ፈርጦች… ፋና ላምሮት የምዕራፍ 22 የድምጻውያን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል More Stories የእናት ውለታዋ … ብዙነሽ በቀለ May 10, 2026 በሙዚቃዎቹ ፍቅር እና እርቅን ሲሰብክ የኖረው አሊ ቢራ… May 7, 2026 ሁለቱ የጥበብ ፈርጦች… May 7, 2026

የእናቶች ቀን, የእናት ፍቅር, ታሪካዊ አመጣጥ, አና ጃርቪስ, የቤተሰብ እሴቶች, እናትነት

Secret Link