ethiopia news

Week 31 Disciplinary Decisions Unveiled

The Ethiopian Football Federation’s disciplinary committee has announced a series of suspensions and fines following the intense action of the 31st week.

ፀጋአብ ዮሐንስ (ምድረ ገነት ሽረ) : ክለቡ ከ አዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ31ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 41 ኛ ደቂቃ ላይየተጋጣሚን ቡድን ተጫዋችን በመጥለፍ ግልፅ ግብ ዕድል በማበላሸት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሐ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ተመስገን ተስፋዬ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ31ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 84 ኛ ደቂቃ ላይየተጋጣሚን ቡድን ግልፅ የግብ የማግባት ዕድል በማበላሸት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሐ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3ዐዐዐ /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ፀጋ ከድር (ቅዱስ ጊዮርጊስ) : ክለቡ ከ መቐለ 70 እንደርታ ጋር ባደረገው የ31ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 89 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ ነቢል ኑረዲን (አዳማ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል። አርባምንጭ ከተማ-አዳማ ከተማ አዳማ ከተማ-ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማ-ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማ-ነገሌ አርሲ አዳማ ከተማ-ምድረ ገነት ሽረ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። በረከት ግዛው (ፋሲል ከነማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል። ሃዋሳ ከተማ-ፋሲል ከነማ ፋሲል ከነማ-ነገሌ አርሲ ባህርዳር ከተማ-ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡና-ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌትሪክ -ፋሲል ከነማ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። በረከት ሳሙኤል (ሃዋሳ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል። ሲዳማ ቡና-ሃዋሳ ከተማ ሸገር ከተማ-ሃዋሳ ከተማ ሃዋሳ ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና አርባምንጭ ከተማ-ሃዋሳ ከተማ ሃዋሳ ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ ሃዋሳ ከተማ-ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ሃዋሳ ከተማ ሃዋሳ ከተማ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ መቻል-ሃዋሳ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕና-ሃዋሳ ከተማ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2ዐዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። በኃይሉ ግርማ (ምድረ ገነት ሽረ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል። ኢትዮጵያ ቡና-ምድረ ገነት ሽረ ምድረ ገነት ሽረ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡና-ምድረ ገነት ሽረ አዳማ ከተማ-ምድረ ገነት ሽረ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። አዛሪያስ አቤል(ወላይታ ድቻ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ። ወላይታ ድቻ-ድሬደዋ ከተማ ሃዋሳ ከተማ-ወላይታ ድቻ ነገሌ አርሲ-ወላይታ ድቻ ወላይታ ድቻ-አዳማ ከተማ አርባምንጭ ከተማ-ወላይታ ድቻ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ኢትዮ ኤሌትሪክ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ31 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮ ኤሌትሪክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት በፍቃዱ አስረሰኸኝ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ/እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ ምድረ ገነት ሽረ ክለቡ ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ31 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የምድረ ገነት ሽረ ቡድን ተጫዋች የሆኑት ሰለሞን 7/ክርስቶስ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ ሲዳማ ቡና ክለቡ ከሸገር ከተማ ጋር ባደረገው የ31 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሲዳማ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት ተመስገን በጅሮንድ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

Ethiopian football, disciplinary decisions, league suspensions, football news, Ethiopian sports, Week 31, penalty update

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Are you human? Please solve:Captcha


Secret Link