ethiopia news

Visa Opens New Addis Ababa Office to Strengthen Accessibility in Ethiopia

Visa has inaugurated a new office in Addis Ababa aimed at strengthening its footprint and accessibility in Ethiopia and the region.

በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው አዲሱ የሥራ ቦታ ፡ ቪዛ በኢትዮጵያና በቀጠናው ያለውን ተሳትፎና ተደራሽነት ያጠናክራል!. አዲስ አበባ – ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም፤ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት የዓለም መሪ የሆነው ቪዛ (NYSE: V) በአዲስ አበባ አዲስ የስራ ቦታውን አስመርቀዋል ፡ ይህም ኩባንያው ከኢትዮጵያ የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ እና ሰፊው ኢኮኖሚ ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነት የሚያሳይ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ምንም እንኳን ቪዛ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ሲንቀሳቀስ ቢቆይም ፣ አዲሱ ቢሮ በሀገር ውስጥ ያለውን የገበያ ተሳትፎ የሚያጠናክር እና ከስራ አጋሮቹ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያሳድግ ነው። ባለፉት ሦስት ዓመታት ቪዛ በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ ሚና በመጫወት በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ይህንንም፤ ትልቅ የሥራ ቡድን በማቋቋም ፣ አቅሙን በመጨመር እና ስልታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ አሳይቷል። በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተመርቆ የተከፈተው ቢሮ ፡ በምስራቅ አፍሪካ ስድስት ቦታዎችን የሚደግፍ ቀጠናዊ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። ይህ ደግሞ ቪዛ በዘርፉ ያለውን እምነት እና በየቀኑ ከደንበኞቹ ፣ ከአጋሮቹ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ያለውን ፍላጎት ያሳያል። አዲሱ ቢሮ ፡ ተቆጣጣሪ አካላት ፣ ባንኮች፣ የፊንቴክ ተቋማት እና ሰፊው የንግድ ማህበረሰብ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችል ማዕከል ነው። ይህም አስተማማኝ፣ ሁሉንም የሚያሳትፍ እና ፈጠራ የታከለበት የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በገበያው ውስጥ እንዲያድግ ይረዳል ተብሎ ይታሰባል። በዚህ የቢሮ ምረቃ ፡ ከፋይናንስ ዘርፉ የተወጣጡ ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት፣ የተቆጣጣሪ ተቋማት ተወካዮች፣ የባንክ ሥራ አስፈጻሚዎች እና የስራ አጋሮቻችን ተገኝተዋል። በአዲሱ ቢሮ `የሚገኘው በፊፋ ዓለም ዋንጫ ተነሳሽነት የተሳለው የግድግዳ ላይ ስዕል ፣ የቪዛ ዓለም አቀፍ የቪዛ-ፊፋ ፕሮግራም አካል ነው። በኢትዮጵያዊቷ የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ኤፍራታ ብርሃኑ የተሳለው ይህ ስዕል፣ እግር ኳስ ሰዎችን ለማገናኘት ያለውን ልዩ ችሎታ እያከበረ፣ የኢትዮጵያን ባህል፣ ፈጠራ እና ማህበረሰባዊ እሴትን ይንጸባርቃል። ስዕሉ ቪዛ ለፈጠራ ኢኮኖሚ ያለውን ቁርጠኝነት እና ለሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ እና በሀገር ውስጥ መድረኮች የሚሰጠውን ድጋፍ የሚያጎላ ነው። በቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ኃላፊ የሆኑት አቶ ያሬድ እንዳለ እንደተናገሩት “ቪዛ በኢትዮጵያ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት የነበረ ቢሆንም፣ ይህን አዲስ ቢሮ መክፈታችን ከገበያው ጋር የምንገናኝበትን ቀጣዩን ምዕራፍ ያመላክታል። ይህ ስፍራ ከተቆጣጣሪ አካላት ፣ ከባንኮች፣ ከፊንቴክ ተቋማት እና ከአጋሮች ጋር በቅርበት ለመሥራት ያስችለናል፡፡ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ እያደገ ላለው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እና ለፈጠራ ኢኮኖሚው ያለንን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” ብለዋል፡፡ የስዕሉ ምርቃት የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችን እና የፈጠራ ሰዎች አዲስ ተመልካቾችን እንዲያገኙ፣ ክፍያዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲቀበሉ እና ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንዲገነቡ እንዴት እንደሚረዳቸው ያሳያል። ይህም ቪዛ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተሳትፎን ለማጠናከር ካለው ሰፊ ሚና ጋር ይጣጣማል። በቪዛ የደቡብ እና የምስራቅ አፍሪካ ኃላፊ የሆኑት አቶ ማይክል በርነር እንደተናገሩት “አዲሱ የቪዛ አዲስ አበባ ቢሮ በቀጠናው ውስጥ ያለውን ተደራሽነት ማጠናከሩን ያሳያል” ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከኬንያ እና ታንዛኒያ ጋር በመሆን በምስራቅ አፍሪካ ካሉን ዋና ዋና የሥራ ማዕከላት አንዷ ሆናለች። ኢንቨስት ማድረጋችን በገበያው ስላለው አቅም ያለንን እምነት እና ከደንበኞች፣ ከአጋሮች እና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር በቅርበት ለመሥራት ያለንን ፍላጎት ያጠናክራል። ወደፊት እያደግን ስንሄድ፣ በዚህ ዓመት በቀጠናው ውስጥ ተሳታፊነታችንን ይበልጥ እንደምናሰፋ እንጠብቃለን፡፡ ስለ ቪዛ ኃ.የተ.የግ.ማ.. ቪዛ : በዲጂታል ክፍያ ስመጥር የሆነ ተቋም ሲሆን ፡ በዓለም ዙሪያ ከ200 በላይ በሚሆኑ አገራት እና ግዛቶች በሸማቾች ፡ በሻጮች ፡ በፋይናንስ ተቋማት እና በመንግሥት አካላት መካከል የሚደረጉ ግብይቶችን ያቀላጥፋል። ተልዕኳችን እጅግ በጣም ምቹ የሆነ ፡ ፈጠራ የተሞላበት ፡ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ ስርዓት በመዘርጋት ፡ ግለሰቦች ፡ ንግዶች እና ኢኮኖሚን አንድ ደረጃ ከፍ በማድረግ ፡ አለምን በተሳለጠ የገንዘብ ፍሰት ማስተሳሰር መቻል ነው።ለበለጠ መረጃ ፡ ድህረ ገጻችንን (Visa.com) ይጎብኙ!. የመገናኛ ብዙኃን ግንኙነት ብራያን ወሶንጋ [email protected]

Visa Ethiopia, digital payments accessibility, Addis Ababa office, East Africa fintech, Visa FIFA program, regulators and banks

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Are you human? Please solve:Captcha


Secret Link