ethiopia news

Mother’s Grace Celebrated in Addis Ababa: “Much Remains of Her”

On Mother’s Day in Addis Ababa, people highlighted the sacrifices and love of mothers, with “Bunech Barke” described as a fitting tribute.

የእናት ውለታዋ … ብዙነሽ በቀለ – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life!. የእናት ውለታዋ … ብዙነሽ በቀለ On May 10, 2026 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእናትን ውለታ የሚመጥን ስጦታ ባይኖርም ፍቅርና መስዋዕትነቷን ለመዘከር በዛሬው ዕለት የእናቶች ቀን በተለያዩ የዓለም ሀገራት ታስቦ ይውላል። ስለ እናት ብዙ ተዚሟል፣ ስንኝ ተቋጥሯል፤ ከእነዚህ ውስጥ በተለይም ዘመን አይሽሬው የብዙነሽ በቀለ የእናት ውለታዋ ሙዚቃ ይጠቀሳል፡፡ ብዙነሽ በዚህ ዜማዋ እንዲህ ስትል ታቀነቅናለች… የእናት ውለታዋን ባወሳ እወዳለሁ፣ ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ፣ ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመንፈሷ፣ ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ፡፡ ዘጠኝ ወር በሆድዋ፣ ከዚያም በጀርባዋ፣ ጡቷን እያጠባች እኔን ማሳደግዋ፣ ዘወትር ይሰማኛል የእማዬ ድካሟ፣ ጥራ በማሳደግ በሴትነት አቅሟ፡፡ የእናት ውለታዋን ባወሳ እወዳለሁ፣ ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ፣ ወላጅ እናት እኮ ፍፁም ሳትሰለች፣ ከራሷ አስበልጣ ልጇን ትወዳለች፡፡ አባቴ ሞቶብኝ በሕፃንነቴ፣ ደክማ አሳደገችኝ ብቻዋን እናቴ፡፡ ሳይርበኝ ሳይጠማኝ ወይም ሳልታረዝ፣ ነው ያሳደገችኝ እማምይ… የእናት ውለታዋን ባወሳ እወዳለሁ፣ ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ፣ ወላጅ እናት እኮ ፍፁም ሳትሰለች፣ ከራሷ አስበልጣ ልጇን ትወዳለች፡፡ እናቱን የማይወድ ሰው አለ ቢሉኝ፣ ሰው ነው አልለውም አውሬ ነው ባይ ነኝ፣ የዋሂቷ እናቴ እኔን ወላጅቷ፣ እጅግ ይሰማኛል እውነተኛነቷ :: የእናት ውለታዋን ባወሳ እወዳለሁ፣ ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ፣ ወላጅ እናት እኮ ፍፁም ሳትሰለች፣ ከራሷ አስበልጣ ልጇን ትወዳለች፡፡ FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like ቃላት የማይገልጹት የእናት ፍቅር… በሙዚቃዎቹ ፍቅር እና እርቅን ሲሰብክ የኖረው አሊ ቢራ… ሁለቱ የጥበብ ፈርጦች… ፋና ላምሮት የምዕራፍ 22 የድምጻውያን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል More Stories ቃላት የማይገልጹት የእናት ፍቅር… May 10, 2026 በሙዚቃዎቹ ፍቅር እና እርቅን ሲሰብክ የኖረው አሊ ቢራ… May 7, 2026 ሁለቱ የጥበብ ፈርጦች… May 7, 2026

Mother’s Day Addis Ababa, mother’s grace, Bunech Barke song, maternal sacrifice, Ethiopian music tribute, family remembrance

Secret Link