Holy Synod General Assembly Concludes with Key Resolutions

The Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church has concluded its seven-day general assembly, passing various resolutions regarding national peace, church unity, and human rights.
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life!. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ On May 14, 2026 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔችን በማሳለፍ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት፣ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነትና ክብር እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ነው የተጠናቀቀው፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት መጠበቅና ማስጠበቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ተግባር በመሆኑ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ሉዓላዊ ክብሯ ተጠብቆ እንድትቀጥል “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት” ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ እና ምርጫው ለኢትዮጵያውያን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን የሚያስገኝ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት አሳስቧል፡፡ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉም ቅዱስ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ በአመለወርቅ መኳንንት FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የሀገር ውስጥ ዜና በመቅደላ ጦርነት ወቅት በብሪታኒያ የተወሰዱ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ የሀገር ውስጥ ዜና አፍሪካ በዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ በቂ ውክልና ሊኖራት ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሀገር ውስጥ ዜና የመደመር መንግሥት መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም በነገው ዕለት ይመረቃል የሀገር ውስጥ ዜና የኢትዮ-ፈረንሳይ ትስስር ይበልጥ እየጠነከረ ይዘልቃል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት More Stories በመቅደላ ጦርነት ወቅት በብሪታኒያ የተወሰዱ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ May 14, 2026 አፍሪካ በዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ በቂ ውክልና ሊኖራት ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር… May 13, 2026 የመደመር መንግሥት መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም በነገው ዕለት ይመረቃል May 13, 2026 1 of 15,143
Holy Synod, Ethiopian Orthodox Church, Church unity, National peace, Addis Ababa, Synod resolutions