Fertilizery plant finishes in days, key issue resolved

በአጭር ጊዜ የማዳበሪያ ፋብሪካው ተጠናቅቆ የኢትዮጵያ አንዱ ቁልፍ ችግር ይፈታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) – Welcome to Fana Media Corporation S.C Fana: At a Speed of Life!
በአጭር ጊዜ የማዳበሪያ ፋብሪካው ተጠናቅቆ የኢትዮጵያ አንዱ ቁልፍ ችግር ይፈታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) On May 17, 2026 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአጭር ጊዜ ውስጥ የጎዴ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቅቆ የኢትዮጵያ አንዱ ቁልፍ ችግር ይፈታል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎዴ ተገኝተው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል። ከጥቂት ወራት በፊት ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር የነበረን ስምምነት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ምርትን መጨመር አንዱ አንጓ ነበር ብለዋል። ሁለተኛው ደግሞ በጎዴ በዓመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ያለው የማዳበሪያ ፋብሪካ መገንባት መሆኑን አንስተዋል። በወቅቱ ለሕዝብ የገነባው ቃል በ40 ወራት ውስጥ የፋብሪካው ግንባታ ይጠናቀቃል የሚል ነበር ሲሉም ገልጸዋል። ይህንን ሥራ ከጀመርን በኋላ በዓለም ላይ ማዳበሪያ እና ነዳጅ በጣም አስፈላጊ ሆኖ ስለመጣ ጊዜውን ለማሳጠር ከዳንጎቴ ጋር ስንመካከር ቆይተዋልም ነው ያሉት። በዚህም ከ40 ወራት በፊት ሥራውን ጨርሰን ምርቱን ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ለመጠቀም ተስማምተናል ብለዋል። ሥራው በፍጥነት ተጠናቅቆ ከ4 ወራት በኋላ ተመልሰን እንመጣለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ተመልሰን ስንመጣ፤ በአካባቢው ለ5 ሺህ ሰዎች የሚሆን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ይጠናቀቃል ሲሉም ተናግረዋል። በአጭር ጊዜ የፋብሪካው ግንባታ ተጠናቅቆ የኢትዮጵያ አንዱ ቁልፍ ችግር እንደሚፈታ አመልክተዋል። በጎዴ አካባቢ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ደረጃ ከፍተኛ ገቢ ለኢትዮጵያ የሚያስገኙ መሆናቸውንም አስረድተዋል። በምግብ ራስን መቻል ዋነኛ አጀንዳችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ በምግብ ራስን ለመቻል መሬት፣ ውሃ እና ሰው እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። እነዚህ ሁሉም አሉን፤ እነዚህን አቀናጅተን ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ እየሰራን እንገኛለንም ነው ያሉት። በዚህም ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የሚተርፍ ነገር ማድረግ እንችላለን ብለዋል። FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint You might also like የሀገር ውስጥ ዜና የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየርና የምርት ባህልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው – ምክትል ጠቅላይ… የሀገር ውስጥ ዜና የማዳበሪያ ፋብሪካው የሥራ ሂደት ፍጥነት አበረታች ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሀገር ውስጥ ዜና አየር መንገዱ አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወነ ነው – አቶ መስፍን ጣሰው የሀገር ውስጥ ዜና በመዲናዋ 12 ሺህ የሰላም ሰራዊት አባላት ተመረቁ More Stories የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየርና የምርት ባህልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ… May 17, 2026 የማዳበሪያ ፋብሪካው የሥራ ሂደት ፍጥነት አበረታች ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ… May 17, 2026 አየር መንገዱ አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወነ ነው – አቶ መስፍን ጣሰው May 17, 2026 1 of 15,158
Gode fertilizer factory, urea production, Dangote cement, Abiy Ahmed, food self-sufficiency, housing for 5,000